Ethiopia TV +

የቀጥታ ስርጭት, ፊልሞች እና ሙዚቃ

ሓተታ ዘርአ ያዕቆብ : ስለ ሃይማኖት - Hatete zera yaakob: About religion

በኋላም ይህ በቅዱስ መፅሃፍት የተፃፈ ሁሉ እውነት ይሆን? ብየ አሰብኩ፡፡ በጣም አላወኩምና የተማሩና ተመራማሪ ሰዎች እውነቱን እንዲነግሩኝ ሄጄ ልጠይቃቸው ብዮ ብዙ አሰብኩ፣ እንደገናም ሰዎች በየልባቸው ያለውን ካልሆነ በቀር ሌላ ምን ይመልሱልኛል ብየ አሰብኩ፡፡ ሰው ሁሉ የኔ ሃይማኖት እውነተኛ ናት ይላል፡፡ በሌላ ሃይማኖት የሚያምኑ ሐሰተኞች የእግዚያብሔር ጠላቶች ናቸው፡፡ ዛሬም ቢሆን ፈረንጆች ሃይማኖታችን መልካም ናት፣ ሃይማኖታችሁ ግን መጥፎ ናት ይሉናል፡፡ እኛም መልሰን እንዲዚህ አይደለም የናንተ ሃይማኖት መጥፎ የኛ ሃይማኖት ግን መልካም ናት እንላቸዋለን፡፡ እንደገናም የእስልምና፣ የአይሁድ አማኞችን ብንጠይቃቸው እንዲሁ ይሉናል፡፡ በዚህም ክርክር ፈራጅ ማን ይሆናል፡፡ ሰዎች ሁሉ እርስ በእርሳቸው ወቃሾችና ተወቃሾች ሆነዋል፡፡ አንድ እንኳን ከሰው ልጅ የሚፈርድ አይገኝም፡፡ እኔ መጀመሪያ ስለብዙ ሃይማኖቶች ጉዳይ አንድ የፈረንጅ መምህር ጠየኩ፡፡ እሱ ግን ሁሉን እንደራሱ ሀይማኖት አድርጎ ፈታው፡፡ ኋላም አንድ ትልቅ የኢትዮጵያ መምህር ጠየኩ ፡፡ እርሱም ሁሉን እነደ ሃይማኖቱ አድርጎ ተረጎመው፡፡ እስልምና እና አይሁድንም ብንጠይቅ እንዲሁ እንደ ሃይማኖታቸው ይተረጉማሉ፡፡ ታዲያ እውነት የሚፈርድ የት አገኛለሁ? የኔ ሃይማኖት ለኔ ትክክል እንደሚመስለኝ እንዲሁ ለሌላውም ሃይማኖቱ እውነት ይመስለዋል፡፡ ነገር ግን ፅድቅ አንዲት ብቻ ናት፡፡ እንደዚህ እያልኩ አሰብኩ፡፡ ጠቢብና የእውነተኞችም እውነተኛ እኔን የፈጠርክ ሆይ አዋቂ አድርገህ የፈጠርከኝ ሆይ ዳዊት ሰው ሁሉ ዋሾ ነው ካለው በስተቀር በሰው ዘንድ ጥበብና እውነት አይገኝምና አንተ አዋቂ አድርገኝ ብዮ ፀለይኩ፡፡ ሰዎች በዚህ ትልቅ ነገር ነፍሳቸውን ለማጥፋት ስለምን ይዋሻሉ? ብየ አሰብኩ፡፡ የሚዋሹም መሰለኝ፡፡ የሚያወቁ እየመሰላቸው ምንም አያውቁምና የሚያውቁ ይመስላቸዋል፡፡ ስለዚህ እውነትን ለማግኝት ብለው አይመረምሩም፡፡ ዳዊት እንዳለው ልባችን እንደወተት ረካ፡፡ ከአባቶቻቸው በሰሙት ልባቸው ረክቷል፡፡ እውነት ወይም ሀሰት ሊሆን ይችላል ብለው አልመረመሩም፡፡ እኔም ጌታ ሆይ ፈርድህን እንዳውቅ ያሳመንከኝ ይገባኛል አልኩ፡፡ አንተ በእውነት ቅጣኝ፣ በምህረትህም ገስፀኝ፡፡ አንተ አዋቂ አድርገህ የፈጠርከኝ ጥበበኛ አድርገኝ እንጅ የዋሾ መምህራንና የሐጢያት ቅባት እራሴን አልቀባም፡፡ እኔ አዋቂ ብሆን ምን አውቃለው ብየ አሰብኩ፡፡ ከፍጥረት ሁሉ የሚልቅ ፈጣሪ እንዳለ አውቃለሁ፡፡ ከታላቅነቱ የተረፈ ታላላቅን ፈጥሯልና፡፡ ሁሉንም የሚያውቅ ነውና፡፡ ከአዋቂነቱ በተረፈ አዋቂዎች አድርጎ ፈጥሮናልና፡፡ ለርሱ ልንሰግድለት ይገባል፡፡ እርሱ የሁሉ ጌታና ሁሉንም የያዘ ነውና ወደርሱ በፀለይን ጊዜ ይሰማናል፡፡ እግዚያብሄር አዋቂ አድርጎ የፈጠረኝ በከንቱ አይደለም፡፡ እንዲህ አድርጎ የፈጠረኝ እንድፈልገውና እርሱ በጥበቡ በፈጠረኝ መንገድ እንዳውቀው እስካለሁም ድረስ እንዳመሰግነው ነው ብየ አሰብኩ፡፡ ሰዎች ሁሉ ሀሰት
ካልሆነ በስተቀር ስለምን እውነት አይናገሩም ብየ አሰብኩ፡፡
የሰው ፍጥረት ታካችና ደካማ መሰለኝ፡፡ ሰው ግን ፍቅርን ቢወዳትና በጣም ቢያፈቅራት የተሸሸገውንም ፍጥረትን ቢያውቅ ይወዳል፡፡ ይህም ነገር እጅግ ጥልቅ ነውና በትልቅ ድካምና ትዕግስት ካልሆነ በስተቀር አይገኝም፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን፡ “ከፀሐይ በታች ስለተደረገው ሁሉ ጥበብን ለመፈለግና ለመመርመር ልቤን ሰጠሁ፡፡ እግዚያብሔር ለሰው ልጆች እንዲደክሙበት የሰጣቸውን ክፉ ስራ አየሁ” ይላል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ሊመረምሩት አይፈልጉም፡፡ ሳይመረምሩ ከአባቶቻቸው የሰሙትን ማመን ይመርጣሉ፡፡ ነገር ግን እግዚያብሔር ሰውን የምግባሩ ጌታ ክፉ ወይም መልካም የፈለገውን እንዲሆን ፈጠረው፡፡ ሰውም ክፉና ዋሾ መሆንን ቢመርጥ ለክፋቱ የሚገባውን ቅጣት እስኪያገኝ ድረስ ይችላል፡፡ ነገር ግን ሰው ስጋዊ ነውና ለስጋው የሚመቸውን ይወዳል፡፡ ክፉ ይሁን መልካም ለስጋው ፍላጎት የሚያገኝበትን መንገድ ሁሉ ይፈልጋል፡፡ እግዚያብሔር ሰው የፈለገውን እንዲሆን ለመምረጥ መብት ሰጠው እንጂ ለክፋት አልፈጠረውም፡፡ ስለዚህ መምረጥ ክፉ ቢሆን ለቅጣት መልካም ቢሆን ደግሞ የመልካምነት ዋጋ ለመቀበል የተዘጋጀ እንዲሆን እድል ሰጠው፡፡ በህዝብ ዘንድ ክብርና ገንዘብ ለማግኝት የሚፈልግ ዋሾ ሰው ነው፡፡ ዋሾ ሰው ይህን በሐሰተኛ መንገድ ሲያገኝ እዉነት አስመስሎ ሀሰት ይናገራል፡፡ ሊመረምሩ የማይፈልጉ ሰዎች እውነት ይመስላቸውና በእርሱ በፅኑ ሃይማኖት ያምናሉ፡፡ እስኪ ህዛባችን በስንት ውሸት ያምናል? በጽኑ ሃይማኖት ያምናል፡፡ በሃሳበ ከዋክብትና በሌላም አስማት፣ አጋነንት በመሳብና በመርጨት፣ አስማት በማድረግ፣ በጥንቆላ ሁሉ ያምናሉ፡፡ ይህንን ሁሉ መርምረው እውነቱን አግኝተው አያምኑም፡፡ ነገር ግን ከአባቶቻቸው ሰምተው ያምናሉ፡፡ እነዚያስ የፊተኞቹ ገንዘብና ክብር ለማግኝት ካልሆነ በቀር ስለምን ዋሹ? እንዲሁ ህዝብን ሊገዙ የሚፈልጉ ሁሉ እውነት እንነግራቸኋለን እግዚያብሔር ወደናንተ ላከን ይሏቸዋል፡፡ ህዝቡም ያምናሉ፡፡ ከነርሱም በኋላ የመጡት እነርሱ ሳይመረምሩ የተቀበሏትን ያባቶቻቸውን እምነት አልመረመሩም፡፡ ከዛ ይልቅ ለእውነት ለሃይማኖታቸው ማስረጃ ታሪክን፣ ምልክቶችን ፣ ተዓምራትን እየጨመሩ አፀኑት፡፡ እግዚያብሔርንም የሐሰኞች ተካፋይና የሐሰት ምስክር አደረጉት፡፡  

ታዋቂ ልጥፎች

እኛ ተከታታይ ፊልሞችን እና በርካታ የተጨመረ ነጻ ይዘት ወይም የደንበኝነት ምዝገባን የሚያቀርብ ጣቢያ ነው, በእርግጥ በቀጥታ እና በቀጥታ ለመመልከት እና ጥራት ያላቸውን የጥራት ደረጃ ይዘት ለማቅረብ በምናደርጋቸው ጥረቶች እና በጥራት ላይ አናመክርም. የምንሰግበው ነጻ የዥረት አገልግሎት ከሚሰጠን በስተቀር, ተከታታይ ፊልሞችን እና ፊልሞችን ወደ ኮምፒውተርዎ ማውረድ ይችላሉ, ቆይተው ለማየት እንዲያደርጉዋቸው, ለምሳሌ የበይነመረብ ግንኙነት ከሌለዎት. በቀጥታ ወደ ፊልሞች ከመሄድ የተሻለ ይሆናል, ሁሌም አስር ኪሎ ግራም ለ 2 ሰዓታት ፊልም አንፈልግም ማለት ነው, ስለዚህ ጣቢያዎቻችን ለቀኝ እይታ እና ተከታታይ ፊልሞችን ያቀርባሉ, ይህም አንድ ጊዜ ጠቅ በማድረግ ይዘትዎን በጥሩ ጥራት ለመመልከት ያስችልዎታል. እንዲሁም በቴሌቪዥን ወይም በሌሎች የዥረት አገልግሎት ላይ ለሚደረግ ማንኛውም ምርመራ የተመረጠውን በይነመረብ በቀጥታ መመልከት ይመርጣል. አብዛኛዎቹ እነዚህ አገልግሎቶች የሚከፈልባቸው ወይም ጥራት የሌላቸው ናቸው. ጊዜን እና አላስፈላጊዎቹን ፍለጋዎች ለመቆጠብ, በጣም ደጋግመው ጣቢያውን እናምናለን, ስለዚህ አብዛኛዎቹ ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልሞች ቅድመ እይታ ወደ መጀመሪያ ጣቢያችን ይሄድና ከሌሎች ጣቢያዎች በበለጠ ፍጥነት ይሻሻላሉ. ከተለቀቀው ፊልም ወይም ተከታታይ ጋር በጣቢያው ላይ በቋሚነት ለመመልከት ሁሉም ፊልሞች እና ተከታታይ ፊልም ቅድመ-ኮድ ውስጥ ይቀመጣሉ, ስለዚህ ስራዎን ለእርስዎ እየሠራን ስለሆነ በድር ላይ ትርጉሞችን መፈለግ የለብዎትም. የመስመር ላይ ፊልሞች እና ፊልሞች የእርስዎ አዲሱ ፊልም ነው.